በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ማንቸስተር ሲቲን አሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ ማንቸስተር ሲቲን አሸነፈ።

ከቀኑ 9 ሰዓት 30 ላይ በተጀመረው በዚህ ጨዋታ ባለ ሜዳዎቹ ማንቸስተር ሲቲዎች ጋሪ ካሂል ራሱ ላይ ባገባው ጎል ቀዳሚ መሆን ችለዋል።

ይሁን እንጂ ከእረፍት መልስ ያንሰራራው ቼልሲ ዲያጎ ኮስታ፣ ዊልያን እና ሀዛርድ ባስቆጠሯቸው ሶስት ጎሎች 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በዚህም ቼልሲ ፕሪሚየር ሊጉን በ34 ነጥብ መምራት ጀምሯል።