አልማዝ የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት በመሆን ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አልማዝ አያና የፈረንጆቹ የ2016 የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት በመሆን ተመረጠች።

ትናንት በተካሄደው የአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማህበር አመታዊ የሸልማት ፕሮግራም በሁለቱም ጾታዎች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ይፋ ሆኗል።

በ2016 የውድድር አመት የዳይመንድ ሊግ አሸናፊ የሆነችው እና በብራዚሉ ኦሎምፒክ ከ23 አመት በኋላ የ10 ሺህ ሜትርን የአለም ክብረ ወሰን የሰበረችው አልማዝ አያና የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት በመሆን ተመርጣለች።

በወንዶች ጀማይካዊው የአጭር ርቀት ንጉስ ዩዜን ቦልት ተመርጧል።

ቦልት ይህን ሽልማት ሲያገኝም ለስድስተኛ ጊዜ ነው።


ምንጭ፦ ቢቢሲ