ከቀረጥ ነጻ ከውጭ የሚገቡ የግንባታ ግብአቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ደንብ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከቀረጥ ነጻ ከውጭ የሚገቡ የግንባታ ግብአቶች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን ለመቆጣጠር የሚያስችል ደንብ ተዘጋጀ።

የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አደረኩት ባለው ዳሰሳ በግንባታ ስም ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ የግንባታ ግብዓቶች ውስጥ ጥቂት የማይባሉ ከግንባታው ፍላጎት በላይ ከቀረጥ ነጻ ገብተው ለገበያ እየቀረቡ ነው ብሏል።

ግብአቶች በህገ ወጥ መንገድ ለገቢያ በመዋላቸው ምክንያት መንግስት ሊያገኝ የሚገባውን ገቢ ያሳጡ ነው።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ነው የሀገር ሀብት እየባከነ መሆኑን ሚኒስቴሩ ባደረገው የኦዲት ክትትል ያረጋገጠው።

ችግሩን ለመከላከል አሁን ላይ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ምዝገባና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቷል።

ደንቡ በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የደንቡ መውጣት ወደ ሀገር የሚገቡ የግንባታ መሳሪያዎች ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር በማጠናከር በዘርፉ የሚሰሩ ህገ ወጥ አሰራሮችን ማስቀረት ያስቸላል ተብሏል።

 

 

በንብረቴ ተሆነ