ጎግል ማንኛውም ሰው በቀላሉ መተግበሪያዎችን እንዲሰራ የሚያስችል አገልግሎት አስተዋውቋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል ማንኛውም ሰው በፈለገው ጊዜ በቀላሉ መተግበሪያዎችን /አፕሊኬሽን/ ለመስራት የሚያስችል አገልግሎት ይፋ አድርጓል።

መተግበሪያ መስሪያው ማንኛውም ሰው በአነስተኛ ኮድ በፍጥነት መተግበሪያዎችን /አፕሊኬሽን/ ለመስራት የሚያስችል ሲሆን፥ ባሳለፍነው ረቡዕ በፕራይቬት ቤታ ላይ ይፋ መደረጉም ተነግሯል።

የመተግበሪያ /አፕሊኬሽን/ መስሪያው ሰዎች በቀላሉ መተግበሪያዎችን ሰርተው በድርጅት ውስጥ ለተለያዩ ተግባራት እንዲጠቀሙበት የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል።

App_Maker.png

“አፕ ሜከር /App Maker” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አገልግሎቱ፥ በተለይም ስራ ለመስራት መተግበሪያ ለሚያስፈልጋቸው ተቋማት ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑ ነው የተነገረው።

 

ምንጭ፦ www.techworm.net