ኤች.ፒ በፍጥነቱ አሁን ካሉ ኮምፒውተሮች በ8 ሺህ እጥፍ የሚበልጥ ኮምፒውተር መስራቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀውሌት ፓካርድ /ኤች ፒ/ በፍጥነቱ አሁን ካሉ ኮምፒውተሮች በ8 ሺህ እጥፍ ይበልጣል ያለውን ኮምፒውተር ሰርቶ የተሳካ ሙከራ ማድረጉን አስታውቋል።

ኤች ፒ እንዳስታወቀው የኮምፒውተሩ ንድፈ ሀሳብ በኮምፒውተሩ ኮምፒውቲንግ ፕላትፎርም ሴንተር ላይ ፕሮሰሰር ሳይሆን ሜሞሪን በማድረግ የተሰራ ነው።

በዚህም እስካሁን ስራ ላይ ካሉ ኮምፒትሮች ፈጣን የሆነ አዲስ ኮምፒውተር መስራት ችለናል ሲል ኩባንያው አስታውቋል።

የወደፊት የኤች.ፒ ኮምፒውተሮችም በዚህ ሊሰሩ ይችላሉ ነው የተባለው።

አሁን የተገኘው አዲሱ የኮምፒውተር ግኝትም ኮምፒውተሮች ላለፉት 60 ዓመታት ሲመረቱበት የነበረውን ምንገድ ሊቀይር እንደሚችልም ነው እየተነገረ ያለው።

HP_2.jpg

በፕሮሰሰር ቦታ ሜሞሪን በማስገባት የተገኘውን ቴክኖሎጂ በመጠቀምም ኤች.ፒ በቀጣይ አሁን ያለውን ቴክኖሎጂ የመቀየር ሀሳብ እንደዳለውም ተገልጿል።

አዲሱ የኤች.ፒ ሱፐር ኮምፒውተር በአነስተኛ ስፍራ ብዛት ያለውን ዳታ መያዝ እንደሚችልም ተነግሯል።

ኤች.ፒ እንዳስታወቀው፥ አዲሱ ኮምፒውተር አሁን በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ካሉት ኮምፒትሮች በ8 ሺህ እጥፍ ፍጥነት ይበልጣል።

 

ምንጭ፦ www.techworm.net